AMN – ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም

በሰሜን ወሎ ዞን ተሰማርቶ የሚገኘው መተማ ክፍለጦር በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ፅንፈኛውን ቡድን ከነ አመራሮቹ በመደምሰስና በማቁሰል የነፍስ ወከፍ መሳሪያ መማረኩን የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደመወዝ መንግስቴ ተናግረዋል።
ሠራዊቱ በወሰደው የተጠናከረ ርምጃ ከተማው በቡድኑ ቁጥጥር ስር እንዳይውል በማድረግ በርካታ ታጣቂ ሀይል በመደምሰስና በማቁሰል በተጨማሪም ክላሽ ፣ ኋላቀር መሣሪያ ፣ ቦምብ ፣ የክላሽ ጥይት ፣ ትጥቅ መማረክ ተችሏል ሲሉ ዋና አዛዡ አብራርተዋል።

መቶ አለቃ ተሾመ ሰለሞን በበኩላቸው የክፍለጦሩ ሠራዊቱ ከበፊትም ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን ተቋቁሞ በማለፍ የተቃጡበትን የውስጥና የውጭ ጥቃቶች በብቃት እየመከተ ሀገርን ያቆመ ዘብ መሆኑን መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!