AMN- ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አጀንዳ ማሰባሰቢያና ተወካይ መረጣ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
በመድረኩ መክፈቻ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው እንዳሉት፣ የመድረኩ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት ሊያንጸባርቁ ይገባል።
እርስ በእርስ በመነጋገር፣ በመመካከርና መደማመጥ ሀገራዊ አንድነትና ሰላም ለማምጣት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሌላው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ችግሮች በንግግርና በመመካከር እንዲፈቱ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በሐረሪ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደበብ ኢትዮጵያ ክልሎች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ጠቅሰዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው መድረክም የህብረተሰብ ተወካዮች ጉዳዩን በደንብ በመረዳትና በመወያየት ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ እንዲያቀርቡም አሳስበዋል።
በመድረኩ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡