ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ማካሄድ ጀመረ

You are currently viewing ኮሚሽኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ማካሄድ ጀመረ

AMN-ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳስታወቁት በዛሬው ውሎ አጀንዳ በማሰባሰብ ሂደት ዙሪያ በኮሚሽኑ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል።

በመድረኩም በክልሉ ከ12 ዞኖችና ከ96 ወረዳዎች የተውጣጡ ሁለት ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የመንግስት አካላት እንዲሁም ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ሌሎች ተሳታፊ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ እየተካሄደ ባለው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና የኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review