ኮሚሽኑ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሶርቲየም ሰብሳቢ ጋር ተወያየ

You are currently viewing ኮሚሽኑ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሶርቲየም ሰብሳቢ ጋር ተወያየ

AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሶርቲየም ሰብሳቢ እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በኮሚሽኑ ፅ/ቤት በተደረገው ውይይት በሀገሪቱ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ በተሻለ መልኩ ስለሚሳተፉበት ሁኔታና ስለሚኖራቸው ሚና ሀሳቦች ተነስተው መግባባት ተደርሶባቸዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የመግባባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የዛሬው ውይይትም ቀደም ሲል የተደረገውን ስምምነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review