AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም
የምዕራብ ዕዝ አንድ ኮር ተልዕኮውን በሚፈፅምበት ምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል፣አነደድና ጎሳም ወረዳ በፅንፈኛው ሃይል ላይ በወሰደው እርምጃ የተዘረፉ ንብረቶችን ማሥመለስ ተችሏል።
የኮሩ ምክትል አዛዣ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ሙላው በየነ በፅንፈኛው ሃይል ላይ እርምጃ እየወሰደ የሚገኘው ሠራዊት ባሳረፈው ከባድ ምት አንፃራዊ ሠላም በመፍጠር ህብረተሰቡን ከስጋት ነፃ የሚያደርግ ውጤታማ ተግባር ተከናውኗል ብለዋል።
በተደረገው ስምሪት ምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል፣ አነደድና ጎሳም አካባቢ በጥፋት ተግባር ሲንቀሳቀስ በነበረው ፅንፈኛ ላይ ኮሩ በወሰደው እርምጃ የነብስ ወከፍ መሳሪያን ጨምሮ የተዘረፉ ሞተር ሳይክሎችን ማሥመለስ እንደተቻለ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።