ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም ወሳኝ ጉዳይ ነው- ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም

You are currently viewing ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም ወሳኝ ጉዳይ ነው- ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም
  • Post category:ዓለም

AMN ህዳር 16/2017 ዓ .ም

ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም ወሳኝ ጉዳይ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም አስገነዘቡ።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፥ “የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ባለው አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በዚህ ወቅት፥ ለኮንፈረንሱ ተካፋዮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።

መደማመጥና ከድንበር እና ከርዕዮተ ዓለም በላይ የሆኑ አጋርነቶችን መፍጠር መቻል እና በተባበረ ክንድ ለመጪው ትውልድ የብሩህ ተስፋ መንገድ ለመጥረግ ዛሬ ላይ አህጉራዊ አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ሰላም በባህሪው በሰው ሰራሽ ድንበር የማይገደብ፤ የሁላችንም መሆኑን ተገንዝበን፣አፍሪካውያን ለሰላም በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ አለብን ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፥ እኛ አፍሪካዊያን ብዝኃነታችንን ተጠቅመን ጠንካራ አህጉራዊ አንድነት ፈጥረን ለችግሮቻችን አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማበጀት የሚሆኑ ሐሳቦችን አቀናጅተን ወደ ዘላቂ ሰላም የሚያደርሰንን መንገድ መቀየስና መጓዝ ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም ወደ አህጉራዊ ሰላምና ብልጽግና ለሚወስደው መንገድ በአንድነት መቆም እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review