ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጰያ የገነባው ዴታ ማዕከል አለም አቀፍ የመመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት የምስክር ወረቀት አገኘ

You are currently viewing ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጰያ የገነባው ዴታ ማዕከል አለም አቀፍ የመመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት የምስክር ወረቀት አገኘ

ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጰያ የገነባው ዴታ ማዕከል አለም አቀፍ የመመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት የምስክር ወረቀት አገኘ ::

በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ ተገንብቶ ወደ ስራ የገባው ማዕከሉ አለም አቀፍ ምዘና ሲደረግለት ቆይቶ የ ቲር 3 ደረጃን በማሟላት ነው የምስክር ወረቀት ያገኘው።

የዴታ ማዕከሉ ለማንኛውም የመንግሥት እና የግል ተቋም በተመጣጣኝ ዋጋ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ፈጣን እና አስተማማኝ የመረጃ የማቅረብ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር ) ዊንጉ አፍሪካ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የራሱን አቅም ከማሳደግ ባለፈ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ የእድገት ማዕከል ለማደረግ የሚያስችል ስኬት መሆኑን ተናግረዋል።

የዴታ ማዕከሉ ለታማኝነት፣ ለቅልጥፍናና ለአገልግሎት አለማቋረጥ የ ቲር 3 የምስክር ወረቀት ማግኘቱ በዓለም ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነት ከማጎልበት ባለፈ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑን አብራርተዋል።

የዊንጉ አፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶኒ ቮስካርዲስ ማዕከሉ የደረጃ 3 የብቃት መስፈርቶችን ማሟላቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጠንካራ የመረጃ ማዕከል መፍትሄዎችን ለማቅረብ ያለንን የማያወላውል ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብላዋል።

ይህ ስኬት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍን የሚከፍት ነው ያሉት

ዋና ስራ አስኪያጁ ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አቅሟን ለማሳደግ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር ያስችላታልም ብለዋል።

ለዴታ ማዕከል የቲር 3 አለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው ማዕከሉ 99 ነጥብ 982 ከመቶ አሰተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በምንም ምክንያት የማይቋረጥ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review