ዑለማዎች ለሀገር ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

You are currently viewing ዑለማዎች ለሀገር ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

AMN-የካቲት 19/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

በምክር ቤቱ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ዑለማዎች ለሀገር ሰላም እና አንድነት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ጉባዔው አንገብጋቢና ወቅታዊ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ በጥናትና ምርምር የተደገፈ ውይይት አድርጓል።

ለሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች የመከረው የዑለማዕ ጉባዔ 3ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ባለ አስራ ሶስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review