በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
በኢትዮጵያ በርዕደመሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተከትሎ መንግሥት የርዕደ መሬት በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሳ የሚያደርግ ቡድን ማሰማራቱን አስታውቋል።
በሲዳማ ክልል ባጋጠመ የመንገድ የትራፊክ አደጋ ከ 70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በመላው ዓለም በድምቀት ተከብሯል።
የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
አስከፊ አደጋ የደረሰባት ደቡብ ኮሪያ በቦይንግ አውሮፕላኖች ላይ ፍተሻ እንዲደረግ ማዘዟ ተነግሯል።
ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የ2.5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፅድቀዋል፡፡
አዲሱ የሶሪያ መሪና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በደማስቆ ተወያይተዋል።
እስራኤል በጋዛ በሚገኙ ጤና ተቋማት ላይ ከምታደርገው ተደጋጋሚ ጥቃት እንድትቆጠብ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም አሳስበዋል።
ከስልጣን የታገዱት የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዬኦል እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት የወሰነባቸው ቢሆንም የሀገሪቱ ባለስልጣናት ፕሬዝደንቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ተገልጿል።
እስራኤል ሀውቲዎች የሀማስ እና ሄዝቦላ እጣፋንታ ሊያጋጥማቸው ይችላል ስትል አስጠንቅቃለች።
ዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን የጦር እስረኞች ልውውጥ አድርገዋል።
ሩሲያ በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ መላክ ማቆሟን አስታውቃለች።
ሩሲያ የአሜሪካ ሰራሽ ሚሳይሎችን ማክሸፏን አስታውቃለች።
አይቮሪኮስት የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።
በአሜሪካ ኒውኦርሊያንስ አንድ ግለሰብ አዲስ አመትን ለማክበር በተሰባሰቡ ሰዎች ላይ በመኪና ባደረሰው ጥቃት ከ14 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል።
እስራኤል የተቋረጠውን የጋዛ ተኩስ አቁም ድርድር ዳግም ለማስጀመር ልኡኳን ወደ ዶሃ ልትልክ መሆኑ ተነግሯል።
አሜሪካ ለእስራኤል 8 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ማቀዷን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ቻይና የኮቪድ መረጃን ይፋ እንድታደርግ የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል።
AMN-ታህሣሥ 27/2017 ዓ.ም