ዓመታዊው የባሎንዶር ሽልማት ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ላይ ይሰጣል

You are currently viewing ዓመታዊው የባሎንዶር ሽልማት ዛሬ ምሽት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ላይ ይሰጣል
  • Post category:ስፖርት

AMN-ጥቅምት 18/2017

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ እየተሰጠ የሚገኘው ባሎንዶር በ68ኛው የእውቅና መስጠት መርሐ-ግብር ዛሬ ምሽት የ2023/24 አሸናፊዎችን ያሳውቃል፡፡

በዓመቱ ምርጥ ወንድ ተጨዋቾች 30 የመጨረሻ እጩዎች ቀርበው ዛሬ አሸናፊው ይታወቃል፡፡

የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ቪኒሲየስ ጁኔር ከማድሪድና ብራዚል ጋራ ያሳካቸው ድሎች ለማሸነፍ ቀዳሚውን ግምት አስገኝተውለታል፡፡

የክለብ አጋሮቹ ጁድ ቤሊንግሃምና ክሊያን ምባፔ እንዲሁም የማንችስተር ሲቲው ሮድሪ ተፎካካሪዎቹ ናቸው፡፡

በሴቶች ምርጥ ተጫዋች፣ በሁለቱም ጾታ ምርጥ ግብ ጠባቂ፣ በምርጥ ወጣት ተጨዋችነት፣ በምርጥ አሰልጣኝነት፣ በምርጥ ክለብ፣ በገርድ ሙለር በተሰየመው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እንዲሁም በሶቅራጥስ በተሰየመው ሰብዓዊነት አሸናፊ የሚሆኑ ተጨዋቾችና አሰልጣኞች ዛሬ ምሽት ፓሪስ ላይ እውቅናቸውን ይረከባሉ፡፡

ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክሪስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ ቢያንስ አንዳቸው እንኳ የሌሉበት የባሎንዶር ሽልማት ነው ዛሬ የሚሰጠው፡፡

የመጨረሻ እጩዎች ከታወቁ በኋላ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችና አምበሎች፣ የተወሰኑ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እንዲሁም ደጋፊዎች የሰጡት ድምጽ ተቆጥሮ በየዘርፉ ለሚያሸንፉ ስፖርተኞች ዛሬ ምሽት እውቅና እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review