የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ማስቀጠል የሚችል አስተማማኝ የሰላም ሀይል ማፍራት ተችሏል:- ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

You are currently viewing የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ማስቀጠል የሚችል አስተማማኝ የሰላም ሀይል ማፍራት ተችሏል:- ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

AMN- መስከረም 28/2017 ዓ.ም

የሀገራችንን እድገትና ብልፅግና ማስቀጠል የሚችል አስተማማኝ የሰላም ሀይል ማፍራት ተችሏል ሲሉ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቢሾፍቱ የዝግጁነት ማረጋገጫ ማዕከል ተገኝተው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን ኦቨር ሆል ተደርገው የተዘጋጁና በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ በሞድፊኬሽን ተሻሽለው የተሰሩ የሰራዊቱን የግዳጂ አፈፃፀም የሚያሳልጡ የሚካናይዝድ ትጥቆችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ሰራዊቱ ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር የሚለውን የተቋሙን እሴት መሠረት በማድረግ መተኪያ ለሌላት ህይወቱ ሳይሳሳ መስዋእትነትን እየከፈለና ሰላምን እያረጋገጠ የሚገኝ የህዝብ ዋልታና መከታ መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናግረዋል።

ተቋማችን የሚሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእቅዳችን መሰረት ያለምንም እንቅፋት መወጣት የሚችል አስተማማኝ ሀይል አፍርተናል፤ በቀጣይም የውስጥ አቅምን በመጠቀም ወጭ ቆጣቢነትን ባማከለ መልኩ የሰራዊታችንን የዝግጁነት ደረጃ ይበልጥ የሚያረጋግጡ መሰል ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

እነዚህ የዘመኑና የሰራዊታችንን የማድረግ አቅም በእጅጉ የሚያጎለብቱ ትጥቆች ወቅቱን በሚመጥን መልኩ ተሻሽለው የተሰሩ ናቸው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ቀድሞ ወደነበሩበት የምስራቅ ዕዝ ሜካናይዝድ ክፍሎች ሲመለሱ የሠራዊታችንን ክንድ የሚያፈረጥሙ ተጨማሪ አቅሞች እንደሚሆኑም ገልፀዋል።

በ2016 በጀት ዓመት በርካታ የተቋሙን ተልእኮዎች በማቀድና በመምራት በኩል ከፍተኛ ስራ ለሰራው ለመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንና ለመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ሰራዊታችንም በየጊዜው የሚታጠቃቸውን ትጥቆች በጥንቃቄና በእንክብካቤ በመያዝና በማቆየት እንዲሁም ለታለመላቸው አላማ ብቻ በማዋልና እንደተቋምም የሀገራችንን እድገት በማስቀጠል በኩል የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማበርከት ይኖርብናል ነው ያሉት።

ሰራዊታችንም በትጥቅም ሆነ በስነ-ልቦናዊ ዝግጁነቱ ያለውን አቅም በማሳደግ እንደወትሮው ሁሉ ለሀገር ሰላምና ለህዝብ ደህንነት በትኩረት መስራት ይኖርበታል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review