![](https://www.amn.gov.et/wp-content/uploads/2024/12/469850700_1010368904469816_6351981873176993921_n-1.jpg)
AMN-ኅዳር 30/2017 ዓ.ም
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ እንዲሳካ ያለውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአባ ገዳዎች እና ከሃደ ሲንቄዎች ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
ለኦሮሚያ ክልል ምክክር ሂደት እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ምን እንደሚመስል እና ለስኬቱም የአባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር፣ አካታች ፣ አሳታፊና ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር እንዲሳካ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ከመንግስት ጋር ያደረጉት የሰላም ስምምነት በመልካም ጎኑ የሚነሳ መሆኑን በመግለጽ በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ አካሄድ እንዲኖር እናበረታታለን ብለዋል፡፡
መሰረታዊና ሀገራዊ በሆኑ የሀሳብ ልዩነቶች ላይ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው እንዲመክር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
ጦርነት እና ግጭት ይብቃ በማለት ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረት የሚበረታታ ነውም ብለዋል።
በዳንኤል መላኩ