የህብረት ስራ ማህበራት ለአሰራር አመቺ የሆኑ ደንቦችን በማዘጋጀት አየተሰራ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታወቀ

You are currently viewing የህብረት ስራ ማህበራት ለአሰራር አመቺ የሆኑ ደንቦችን በማዘጋጀት አየተሰራ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታወቀ

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

የህብረት ስራ ማህበራት ለአሰራር አመቺ የሆኑ ደንቦችን በማዘጋጀት ዘርፉ የሚፈለገው ደረጃ እንዲደርስ እየተሰራ ስለመሆኑ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ለአሰራር አመቺ ናቸው ያላቸውን ደንቦች በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጎባቸዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ተጫነ አዱኛ ህብረት ስራ ማህበራት ከዚህ ቀደም ባልተደራጀ ህግና ደንብ በመመራት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለአባሎቻቸው መስጠት አለመቻላቸውን አመልክተዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት አዳዲስ ደንቦችን በማዘጋጀት ለተግባራዊነታቸው ከማእከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ግንዛቤ እያስጨበጠ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ተጫነ አዱኛ ገልጸዋል።

በዝናሽ ሞዲ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review