የህዝቡን ግንዛቤ በማሳደግ የአየር ብክለትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ፦ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

You are currently viewing የህዝቡን ግንዛቤ በማሳደግ የአየር ብክለትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ፦ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን የህዝብ ግንዛቤ ተሳትፎ በማሳደግ በጥራትና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የአየር ብክለትን ለመከላከል በትኩረት እተየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ነው።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዲ ዲሪባ በከተማው የህዝብ ግንዛቤ ተሳትፎ በማሳደግ በጥራትና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የአየር ብክለትን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ “በሚል እንደ ሀገር ያስጀመረውን የ6 ወራት ንቅናቄ እየገመገመ ይገኛል።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአከባቢ ጥበቃና ብክለት ማስወገድ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረክ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የፕላስቲክ ልምዶችን እናስወግድ በሚል በአከባቢ ጥበቃና ብክለት ማስወገድ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ የመጣው ለውጥና ያስገኘው ውጤት ላይ ሰፊ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እያካሄደ ያለው ንቅናቄ “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ “በሚል እንደ ሀገር የተጀመረው የ6 ወራት ንቅናቄ ላይ የታየ ክፍቶችን በማረም ለቀጣይ የንቅናቄ

መድረኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ዋና ስራ አስኪያጁ እንደ ሀገር እየተካሄደ ያለው የፅዳት ንቅናቄና የተጀመሩ ተግባራት ፅዱ ከባቢን ለመፍጠር ትልቅ አቅም አላቸው ብለዋል፡፡

በሃይል አማራጮች ላይ በማተኮር የኢነርጂ ቆጣቢነትን ማሳደግ ፣ የታዳሽ ሃይልን ማስተዋወቅ እና ለከተማዋ የማይበገር የኢነርጂ ስርዓት በመፍጠር ለአረንጓዴ ልማት አስተዋፅኦ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ለስድስት ወራት የተጀመረው የብክለት ማስወገድ ንቅናቄ በፕላስቲክ ፣በአየር ብክለት ፣በውሃ ብክለት እንዲሁም የአፈር ብክለት ላይ የህዝቡን ግንዛቤን ለማሳደግ በየወራቱ የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተመላክቷል።

የወንዝ ዳርቻ ልማትን በማንሳት ከተማ አስተዳደሩ የጀመራቸው የአከባቢ ፅዳት ስራ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አቶ ዲዳ ተናግረዋል።

በመሀመድ ኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review