የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

You are currently viewing የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

AMN – ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው፣ የምክር ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ የሚያጽደቅ ሲሆን ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታየ አፅቀስላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ማዳመጥ እና የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ፣ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ፣ የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review