AMN – ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
በመደበኛ ስብሰባው የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣ የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ሹመታቸው የጸደቀላቸው ከፍተኛ አመራሮች ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን ምክር ቤቱ ካዳመጠ በኋላ አፅድቋል።