AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም
የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት ዘመቻ ተከናውኗል፡፡
የፅዳት መርሐ ግብሩ በኦሮሞ ባህል መሰረት በአባገዳዎችና በሀደሲንቄዎች በምረቃ ስነ ሰርዓት ተጀምሯል።
ፅዳቱን ያስጀመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣ ኢሬቻ ሰላም በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ለሰላምና ለአብሮነት ያለንን ቁርጠኝነት በማሳየት ነው ብለዋል።
የፅዳት መርሐግብሩ የጋራ አብሮነታችንን የምናሳይበት ነውም ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው ፣ የኢሬቻ በዓል ፈጣሪ የሚመሰገንበት በመሆኑ ሁሉም ተቀራርቦ አብሮነትን ከፍ በማድረግ ሊያከብረው እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመረኃ ግብሩ ላይ አባገዳዎች፤ ሀደ ሲንቄዎች፤ የኃይማኖት አባቶች እና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ታዳሚ ሆነዋል፡፡
የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ቅዳሜ መስከረም 25/2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን ለበዓሉ አዲስ አበባ ከተማ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጁ ሆና እየተጠባበቀች ነው፡፡
በአልማዝ ሙሉጌታ