የሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ቅዳሜ ይፈጸማል

You are currently viewing የሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ቅዳሜ ይፈጸማል

AMN- ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

የሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ቅዳሜ እንደሚፈጸም ቫቲካን አስታውቃለች።

ፖፕ ፍራንሲስ “ከባድ ስትሮክ እና ሊመለስ የማይችል የልብ ችግር አጋጥሟቸው” በትናንትናው ዕለት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወቃል።

ካርዲናሎች በዛሬው ዕለት በቫቲካን ተሰብስበው የፕፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር የሚፈፀምበትን ቀን ወስነዋል።

በዚህም አስክሬናቸው በነገው ዕለት በከተማዋ ወደሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ተወስዶ እስከ ዕለተ ቀብራቸው ድረስ ምዕመኑ በስፍራው በመገኘት እንደሚሰናበታቸውም ተገልጿል።

የሊቀ ጳጳሱ ሞት በዓለም ዙሪያ ባሉ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከባድ ሀዘን የፈጠረ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ ሳምንታት አዲስ መሪ ትመርጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review