AMN- የካቲት 7/2017 ዓ.ም
የሊቢያ መንግስትና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ብሔራዊ የሰላምና እርቅ ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረትና አደራዳሪ ኮሚቴው እንዳስፈጸሙት ተገልጿል፡፡
በዚሁ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት ባስተላለፉት መልዕክት አፍሪካን ከሰላም እጦት ለማላቀቅ ህብረቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው እሳቤ የውስጥ ችግሮችን መፍታት አንዱና ዋነኛው ግብ መሆኑንም አብራርተዋል።
ሊቢያን ወደ ቀደመ ሰላሟ ለመመለስና የዜጎቿን ደህንነት ለማረጋገጥ የአፍሪካ ህብረት አስማሚ ኮሚቴ አቋቁሞ የማወያየት ስራ ሲያከናወን መቆየቱን አስታውቀዋል።
ኮሚቴው ያቀረበው የስምምነት ሰነድ ሁለቱንም አካላት በፍትሃዊነት የዳኘና ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል።
ለስምምነቱ ተፈፃሚነት የሊቢያ መንግስትም ሆነ የተፎካካሪ ፓርቲ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ ላይ የሚሰሩ አለም አቀፍ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በስምምነቱ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።