የሐረሪ መስተዳድር ምክር ቤት ከጥቅምት ወር ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በአዲሱ ጭማሪ እንዲከፈል ወሰነ

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሕግን በተከተለ አግባብ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ የውሳኔ ሀሳብ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ተመንን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው በመወያየት ውሳኔ ያሳለፈው።

በዚህም መስተዳድር ምክር ቤቱ በመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ላይ በመምከር ካለፍው የጥቅምት ወር ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዝ ጭማሪ ህግን በተከተለ አግባብ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ አሰልፏል።

የመስተዳድር ምክር ቤቱ በመቀጠል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ተመንን ለማሻሻል በቀረበ የመስተዳድረ ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ላይ ሰፊ ውይይት አካዷል።

መስተዳደር ምክር ቤቱ ባካሄደው ውይይት ደንቡ ከመስተዳደር ምክር ቤቱ አባላት የተሰጡ አስተያየቶችን አካቶ ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረው የአገልግሎት ክፍያ ዋጋ የቆየና ዝቅተኛ በመሆኑ ከክልሉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ጋር የተጣጣሙ ባለመሆናቸው ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ መመላከቱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

All reactions:

4747

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review