የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ እንደሚገባ ተመላከተ

You are currently viewing የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ እንደሚገባ ተመላከተ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የማዘጋጀት ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ ለመስጠት ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የቅንጅታዊ ፎረም የስድስት ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ፣ በበጀት አመቱ በሶስቱም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል እና ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ አኳያ የተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ከተማዋ በዚህ ረገድ የደረሰችበትን ደረጃ በይበልጥ የሚያሳይና አበረታች እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡

ምክትል ስራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ በተቋማቱ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም አሁን ካለበት በተሻለ ፍጥነትና ጥራት በማጠናቀቅ ፕሮጀክቶቹ የታለመላቸውን ጠቀሜታ እንዲያበረክቱ ከማድረግ አንጻር ከተቋማትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተሻለ ቁርጠኝነት፣ ተነሳሽነትና ቅንጅታዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review