የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የተጀመረዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን አይተናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የተጀመረዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን አይተናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ጋር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ስራን ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ ጉብኝቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን 16 ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለይቶ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውሰዋል።

ከነዚህ ተቋማት መካከል የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የተጀመረዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተለይም እስከ ዛሬ ድረስ የተፈጠሩ መብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ መብቶችን በግልፅነትና በታወቀ ውሳኔ ብቻ መብት እንዲፈጠር የማድረግ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ፋይል በፎርጂድ ተደራጅቶ ሲመጣ ወደ ሲስተም እንዳይገባ የመከላከል፣ በተጭበረበረ እና በህገወጥ መንገድ መብት ፈጠራን የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም በህገ ወጥ መንገድ መብት ቢፈጠር እንኳን በቀላሉ ውድቅ የሚሆንበት፣ ለጀርባ ማህተም ተገልጋይ የማይንገላታበት፣ የደብዳቤዎች ስወራን እንዲሁም ከሰው ማህደር ውስጥ ፋይል ማጥፋትና በህገወጥ መንገድ ፋይል የመጨመር እና ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን በሚያስቀር ደረጃ የተሟላ የዲጂታል ስራ እየተተገበረ እንደሚገኝ ከንቲባዋ አስታውቀዋል።

ተገልጋዮች ይህ ከፍተኛ እንግልት የነበረበት አገልግሎት፣ እንግልቱ ቀንሶ ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ ካልሆነ በስተቀር በያሉበት ቦታ ሆነው መገልገል የሚችሉበትን ስርዓት መዘርጋቱን የገለጹት ከንቲባዋ አገልግሎቱን በመረዳት በህጋዊ መንገድ መገልገል እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

አገልግሎቱን ከዚህ በላይ የላቀ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲስተሙን እኩል መጠቀም እንዲችሉ እነሱንም የማናበብ ስራ እየሰራን እንገኛለንም ብለዋል፡፡

አሁን የሊዝና የመሬት አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ሁሉም ክፍያዎች ግለሰብ ጋር ሳይደርስ በባንክ እና ቴሌብር በኩል እንዲከፈል ማድረግ ስለተቻለ ተገልጋዮች እንዲገለገሉበት ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንን መልካም ጅማሮ ተደራሽ ለማድረግ ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review