የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ነዋሪዎች ገለጹ

You are currently viewing የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ነዋሪዎች ገለጹ

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቱፊታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የፍቅር መገለጫ የሆኑትን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን በጋራ ለማክበር የሚያስችል የዉይይት መድረክ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።

አዋሳኝ በሆኑት በሸገር ከተማ ከኮዬ እና ከገላን ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች እና ነዋሪዎች በበዓሉ ስኬታማነት ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ ምክክርም እያደረጉ ይገኛሉ ።

የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቱፊታቸዉን ጠብቀዉ ይከበሩ ዘንድ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ተሳታፊዎች ተናግረዋለ።

በሩዝሊን መሀመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review