የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፦ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ

You are currently viewing የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በስኬት እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፦ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ

AMN- መስከረም 10/2017 ዓ.ም

የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጀ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አስታውቀዋል።

የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የፍቅር መገለጫ የሆኑትን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን በጋራ ለማክበር የሚያስችል ዉይይት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ከሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ፋይዳቸው በተጨማሪ ዲያስፖራዎች ፣ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚሳተፉባቸው የሀገር ሀብት ናቸው ሲሉም ነው ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ያስገነዘቡት።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው የበዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለሀገረ መንግስት ግንባታው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቅንጅታዊ ርብርቡ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ወጣቶችና በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ተገኝተዋል።

የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በዓላቱ በሰላም ተጀምረው በሰላም እንዲጠናቀቁ ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

በመሀመድ ኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review