የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ

You are currently viewing የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ

AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም

እድሳቱ ሁለት ዓመታትን የፈጀው የታሪካዊዉ የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ዛሬ ተመርቋል ፡፡

ህንፃ ቤተ ክርስቲያኑን መርቀው የከፈቱት ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ወ እጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሀይማኖት ናቸው።

መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን 81 አመታትን ያስቆጠረ ባለ ታሪክ ቤተክርስቲያን ነው።

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊነቱን በጠበቀ መልኩ ዕድሳት እንደተደረገለትም ተጠቁሟል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አክኪያጅና የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የቡራኬ ቤተ ክርስቲያኑ ሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል።

በቀደመ ስሙ መካነ ሥላሴ በኋላ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተባለው ይህው ቤተ ክርስትያን የዛሬ 81 ዓመት በግርማዊ ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጥር 7ቀን 1936 ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ መከበሩን መረጃዎች ያስረዳሉ።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review