የመንግስት ተቋማትን የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ መገምገም ጀምረናል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የመንግስት ተቋማትን የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ መገምገም ጀምረናል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

የመንግስት ተቋማትን የመጀመሪያ ሩብ አመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕቅድ አፈጻጸም ዛሬ መገምገም መጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

በቆይታቸውም በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ አበይት ተግባራት ላይ የተገኙ ዉጤቶችን እና የታዩ ክፍተቶችን ከተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እንደሚያዩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ለሚንስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደተደረገበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሪፎርሙን ውጤት ለማስቀጠልና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቀጣይ ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡

“በዚህ ሩብ አመት ሀገራችን ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የገባችበት በመሆኑ በዚሁ መድረክ ለየት ባለመልኩ የታዩ ለውጦችን እንዲሁም ፈተናዎችን በተሟላ ሁኔታ ማሳየት የሚያስችል ግምገማ እናካሂዳለን” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review