የመጀመሪያው የአፍሪካ የወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የመጀመሪያው የአፍሪካ የወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

AMN – ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

በስርዓተ ምግብና በስርዓተ ግብርና ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው “ታውዘንድስ አፍሪካ” የወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጉባዔ ከ45 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ 250 ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ለ3 ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ የግጭት አፈታት፣ የግብርና ቴክኖሎጂን ማዘመንና ብዝሀ ህይወት ጥበቃ እንዲሁም አገር በቀል እውቀቶች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል።

በጉባዔው ላይ የተገኙት የኘላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አሰፋ አፍሪካ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ ድርሻ ቢኖራትም በለውጡ ምክንያት ዘርፈ ብዙ ቀውስ እያስተናገደች ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋም በምታደርገው ጥረት በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በርካታ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኗን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ መቻሏን አንስተዋል።

የአህጉሪቱ ወጣቶች አገር በቀል እውቀቶችን በማሳደግ የአካባቢያቸውን የአዝዕርት ዝርያዎችን በጠበቀ መልኩ ግብርናን ማዘመን ላይ እንዲያተኩሩ በጉባዔው ላይ ጥሪ ቀርቧል።

በትዕግስት መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review