አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 የኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ባለሞያዎች ማህበር ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የኡለሞች ጉባኤ ጋር የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የሸሪዓ አማካሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ አካሂዷል።
በጉባኤው የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችን መሰረት አድርገው የሚሰሩ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች እና የማይክሮ ፋይናስ ተቋማት ተሳትፈዋል።
ጉባኤው ባንኮች በተናጠል የሚሰጡትን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ወጥ የሆነ የፋይናንስ ስርዓት በመዘርጋት ወጥነት ያለው የባንክ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያግዝ ነው ተብሏል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገው በዚህ ጉባኤ ላይ የወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች እና አጠቃላይ አሠራሩን በተመለከተ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።