የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ እና የመሬት ማግኔታዊ መስክ መለኪያ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

You are currently viewing የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ እና የመሬት ማግኔታዊ መስክ መለኪያ መሳሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በአንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል ከደቡብ አፍሪካው አቻ ተቋም ጋር በመተባበር የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ እና የመሬት ማግኔታዊ መስክ መለኪያ መሳሪያ ተከላን አጠናቆ ወደ ስራ አስገብቷል።

ወደ ትግበራ የገባው የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በተለምዶ ጂፒኤስ ብለን ከምናውቀው እና ከሌሎችም መሰል አገልግሎት ከሚሰጡ ሙሉ የዓለም ሽፋን ካላቸው የሳተላይት መገኛ ስርዓቶች መረጃ መቀበል የሚያስችል ነው፡፡

በተመሳሳይ የማግኔታዊ መስክ መለኪያ መሳሪያው (ማግኔቶሜትር ) የመሬት ማግኔታዊ መስክ በጊዜ ውስጥ የሚኖረውን ለውጥ ካለማቋረጥ መለካት የሚያስችል መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በተለይም መዲናችን አዲስ አበባ Magnetic Equator ተብሎ የሚታወቀው መስመር በቅርብ ርቀት ከሚያልፍባቸው የዓለማችን ስፍራዎች አንዷ ከመሆኗ ጋር ሲታይ የመሳሪያው በእንጦጦ ተራራ ላይ መተከል በሂደት የዓለም አቀፉ የማግኔቶሜትር ትስስር መረብ አንድ አካል የመሆናችንን እድል የበለጠ ያሰፋዋል ተብሏል፡፡

ከዚህ መሳሪያ እና ከላይ ከተጠቀሰው ጣቢያ /GNSS/ የሚገኘው መረጃ ከሌሎች አገልግሎቶች በተጨማሪ ኢንስትቲዩቱ እያደራጀው ላለው የሰፔስ ዌዘር መከታተያ ማዕከል ወሳኝ ግብዓት ሆነው እንደሚያገለግሉም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review