AMN – ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ ነበር ።
ይኽን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ስብሰባ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተካሂዷል።
በስብሰባው የመስክ ምልከታና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን ማቅረባቸው ተመልክቷል።
የሱፐርቪዥን እና የግብረመልስ ሂደት ሰፋ ያለው ሥርዓትን የማጠናከር ተግባር አካል ሲሆን አፈፃፀሞችን በዞን እና ወረዳ ደረጃ በመመልከት ክፍተቶችን መለየትን አላማ ማድረጉን የፅህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።