AMN – ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም
የማህበራትን ሀብት ከብክነት የመታደግ ምዕራፍን አልፈን ወደ ማዘመን ምዕራፍ ተሻግረን የሚታይና ተስፋ ሰጭ ስራዎችን ማከናወን እየተቻለ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ልእልት ግደይ ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሯ የሁለተኛ ዙር ሪፎርም ትግበራ ስራዎችን ከዘርፉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ገምግመዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የሪፎርም ትግበራ ስራዎቻችንን በሚገባ አጠናቀንና ለሁለተኛው ዙር የሪፎርም ስራዎቻችን መደላደል ከሆኑት አንዱን ደንብ ቁጥር 170/171ን በማፅደቅና በየደረጃው ላለው አመራርና ሠራተኛ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት ወደ ተግባር መገባቱን አውስተዋል፡፡
የማህበራትን ሀብት ከብክነት የመታደግ ምዕራፍን አልፈን ወደ ማዘመን ምዕራፍ ተሻግረን የሚታይና ተስፋ ሰጭ ስራዎችን ማከናወን እየተቻለ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ከኪራይ ነፃ በማድረግና ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም አቅም በፈቀደ መጠን የከተማዋን ስታንዳርድ የሚመጥን አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በፓይለት ደረጃ እየተተገበረ እንደሆነም ነው የገለፁት፡፡
ከኮሪደር ልማት በተያያዘ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ተነሽ ለሆኑ ማህበራት ምትክ ቦታ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ያወሱት ክብርት ኮሚሽነር የዘርፉ አመራሮች በቂ መረጃ መያዝ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
አስከ አሁን ባለው ሂደት ከኪራይ ነፃ በማድረግ ለፍሬሽ ኮርነር፣ ለህፃናት መጫወቻ፣ ለመዝናኛ፣ ለፕሮሰሲንግና ሌሎችም ግልጋሎት መስጠት የሚችሉትን የመለየትና አንዳንዶቹ ደግሞ ወደ ስራ የማስገባት ስራ እንደተሠራም ነው የገለፁት፡፡
የዘርፉ አመራሮችም የተሰጣችውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡ በመጨረሻም በቀጣይ መስራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
All reactions:
68Tsehhay Habte, Us Man Mohammed and 66 others