የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ይዛ የተሰወረችው አውሮፕላን ስብርባሪ መገኘቱ ተገለጸ

You are currently viewing የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ይዛ የተሰወረችው አውሮፕላን ስብርባሪ መገኘቱ ተገለጸ
  • Post category:ዓለም

AMN – ሰኔ 4/2016 ዓ.ም

የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎችን ይዛ መሰወሯ የተነገረው የጦር አውሮፕላን ስብርባሪ መገኘቱን እና በስፍራው በሕይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቼክዌራ ገለጹ።

አይሮፕላኗ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ የአየር ንብረት ክልል ስትበርር እንደነበር ተገልጿል።

የአውሮፕላኗ ስብርባሪ የተገኘው ቺካንጋዋ የተባለ ጫካ ውስጥ የሀገሪቱ ጦር ሀይል ባደረገው አስቸጋሪ ፍለጋ በኋላ ነው ተብሏል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቼክዌራ የምክትል ፕሬዚዳንቱ እና ሌሎች አባላት በሕይወት አለመትረፍ ለማላዊያን ሳሳውቅ በከፍተኛ ኀዘን ውስጥ ሆኜ ነው ብለዋል።

የ51 ዓመቱ ሳውሎስ ቺሊማ እና ሌሎች 9 ሰዎች ከዋናው ከተማዋ ሊሎንዌይ በትናትናው ዕለት ከማለዳው ሦስት ሰዓት በረራ የጀመሩ ሲሆን ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አውሮፕላኗ ከራዳር ውጪ በመሆን ግንኙነቷ እንደተቋረጠ ተመልክቷል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቼክዌራ በትንትናው ዕለት የሀገሪቱ ጦር ኃይል አውሮፕላኗ እንዲፈልግ ጥብቅ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን ገልጸው አሁን ላይ በፍለጋው የአውሮፕሏኗ ስብርባሪ እንደተገኘ እና በሕይወት የተረፈ እንደሌለ ለሀገሪቱ ቴሌቭዥን ባስተላለፉት መግለጫ አመልክተዋል። ዘገባው የቢቢሲ፣ አልጀዚራ እና ሬውተርስ ነው።

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review