የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብ 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባላፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ እንዳሳየ ጠቁመዋል፡፡

በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን በማንሳት ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ይህም የወርቅ ምርት ምን ያህል ለህገ ወጥ ንግድ ተጋልጦ እንደነበር የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review