የማይስ ኢንደስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ የሚያበረክት የዳበረ ኩነት ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግስት ቁርጠኛ ነው-የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ

You are currently viewing የማይስ ኢንደስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ የሚያበረክት የዳበረ ኩነት ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግስት ቁርጠኛ ነው-የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ

AMN-ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ከኹነት አዘጋጆች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በቱሪዝም ሚኒስትር በተካሄደው ውይይት ላይ የትብብር እድሎች፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች እና ኢትዮጵያን ዋና የማይስ መዳረሻ ለማድረግ በሚበጁ ጉደዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የማይስ ኢንደስትሪ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ የሚያበረክት የዳበረ ኩነት ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት በአጽንኦት ገልፀዋል።

የድርጅቶቹ ተወካዮች በኢንዱስትሪው ፍላጎቶች ላይ ያሉ አጠቃላይ ግንዛቤያቸውን በማካፈል በአፍሪካም ይሑን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ከመውጣት አንጻር በተግዳሮትነት የሚነሱ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

ሚንስትሯ የቱሪዝም ሚኒስቴር የሀገራችንን ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ መገንባታ ዋና ሥራው በመሆኑ የዘርፉን እድገትን የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን መመሪያዎችን በማዘጋጀት እና ወደ ተግባር እንዲገቡ በማድረግ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መደበኛ በሆነ የግንኙነት አግባብ በመፍጠር አጋርነትን ለማጎልበት እንደሚያስፈለግ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review