የሠላም ስምምነቱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና ለህዝብም እፎይታ የሚሰጥ ነው፡- የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

You are currently viewing የሠላም ስምምነቱ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና ለህዝብም እፎይታ የሚሰጥ ነው፡- የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

AMN – ታኅሣሥ -8/2017 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ያደረገው የሠላም ስምምነት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና ለህዝቡም እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ገለጹ።

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼኽ ጋሊ ሙክታር እንደገለጹት፤ የኅብረተሰቡን የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና አብሮ የመኖር ባህል እንዲጠናከር የኃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው።

ሠላምን በማስፈን ረገድ ምክር ቤቱ ከኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በቅርቡ የክልሉ መንግሥት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር የደረሰው የሠላም ስምምነት ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የሚበረታታ እርምጃ ነው ብለውታል።

ባለፉት ዓመታት በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሠላም ችግሮች የዜጎችን ሕይወት አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበር አስታውሰው፤ የተደረሰው የሠላም ስምምነት ይህን ሁኔታ በመቀየር ለህዝቡ እፎይታ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ለረጅም ጊዜ የሠላም ስምምነት እንዲፈጠር የተደረገው ጥረት ውጤት እያመጣ መሆኑን የአሁኑ ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል።

በቀጣይ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በቀጣይ ዘላቂ ሠላም በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰፍን ጥረቱ ይበልጥ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ ነፍጥ ያነሱ ኃይሎች ልዩነታቸውን በሠላም እንዲፈቱ ሁሉም አካል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር የተደረሰው ሥምምነት ተግባራዊነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review