የሠራዊታችን ጥንካሬ የሀገር ጥንካሬ ነው:- አይሻ መሀመድ

You are currently viewing የሠራዊታችን ጥንካሬ የሀገር ጥንካሬ ነው:- አይሻ መሀመድ

AMN-ጥቅምት 15/2017 ዓ/ም

የሠራዊታችን ጥንካሬ የሀገር ጥንካሬ ነውና መላው ህዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ሊቆም ይገባል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ( ኢንጂነር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

117ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን “በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ ሠራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር) በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ ሠራዊቱ ለሀገሩ የከፈለውና እየከፈለ ላለው ዋጋ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በፈተና ያለፈ የማይናወጥ ቁርጠኝነት የተላበሰ ሠራዊት በመሆኑ እንዲህ ባለው ቀን ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ሀገርን የመከላከልና የመጠበቅ ሥራ መቼም ቢሆን የሚያበቃ አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ፤ ሰራዊቱ እረፍት የማያውቅ ቁርጠኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይህን የማያልቅ ሃላፊነት የተሸከመው ጀግናው ሠራዊትም የጥንካሬ ተምሳሌት ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል፡፡

የሀገር ደህንነት የሚረጋገጠው በጦርነት በሚገኝ ድል ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ባለው የማያቋርጥ ዝግጁነት በመሆኑ ሠራዊቱም ባለው ዝግጁነት ሁሉም ኩራት ሊሰማው ይገባል ነው ያሉት፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሠራዊቱ አባላት ፣ አባት ዓርበኞች፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የሠራዊቱ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review