የሩሲያ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ

You are currently viewing የሩሲያ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ

AMN – ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

የሩሲያ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ እና በሀገሪቱ ገበያ ምርታቸውን በስፋት ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።

በብሪክስ ጉባዔ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሩሲያ ታታርስታን ግዛት ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ጋር የቢዝነስ ፎረም አካሂዷል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱም (ዶ/ር) ለኩባንያዎቹ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው የኢንቨስትመት መስኮች እና ስለተዘጋጁ ማበረታቻዎች ገለጻ አድርገዋል።

ብሪክስ ይዞት የመጣውን ዕድል በመጠቀም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የታታርስታ ግዛት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስትር ኦሌግ ኮሮብቼንኮ በበኩላቸው፥ የግዛቱ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

ግዛቷ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና ሮቦቲክስ ዘርፍ ያላትን ከፍተኛ አቅም ወደ ኢትዮጵያ ማስፋት እንደምትፈልግ አረጋግጠዋል፡፡

የኩባንያ ኃላፊዎቹም በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልጉ አስታውቀው፥ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ልዑክ እንደሚልኩ አመላክተዋል፡፡

በብሪክስ ጉባዔ ለመሳተፍ ሩሲያ ካዛን የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ የተለያዩ ኩባንያዎችን መጎብኘቱን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review