የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ ገቡ

AMN- ጥር 21/2017 ዓ.ም

የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።

ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።

በጉባኤ ላይ የሚታደሙ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

በዚህም ማምሻውን የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ አዲስ አበባ መግባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቱሪዝም ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዳው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review