የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሻልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሻልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ጥር 2/2017 ዓ.ም

የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር የፋይናንስ ስርዓቱን የሚያሻሻልና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያግዝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት ልዩ ልዩ የገበያ አይነቶችን የሚያቀርብ ነው፡፡

እነርሱም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስብራት ብሎም የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ከተከናወኑ ስራዎች አንዱ ዲጂታላይዜሽን መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ አማካኝነትም የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓትን ማስፋት መቻሉን ነው ያነሱት፡፡

በአሁኑ ወቅትም 51 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ የተመዘገበውን ስኬት በካፒታል ገበያ ስርዓት በመደገፍ ኢኮኖሚውን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያብራሩት፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድ የሚያንቀሳቅስ፤

ግዙፍ የኃይል ግድብ እንዲሁም እንደ ኢትዮ-ቴሌኮም ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን የገነባ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ይህ ግዙፍ ኢኮኖሚ ለሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ምቹ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያም ውጤታማ እንደሚሆን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት ለውጤታማነቱ ጊዜ ወስዶ ሰፋፊ ጥናቶችን ማከናወኑን በመግለጽ፡፡

በሌላ መልኩ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መጀመር ሃሳብ ኖሯቸው በገንዘብ እጥረት ምክንያት ስራ መጀመር ላልቻሉ ወጣቶችም ሃሳባቸውን አቅርበው ፋይናንስ እንዲያገኙ የሚያደርግ ስለመሆኑም ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review