የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች “ፋይዳ” መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

You are currently viewing የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች “ፋይዳ” መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

AMN – ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review