የሴቶችን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የብድር አገልግሎቶች ማመቻቸቱን ስኬት ባንክ አስታወቀ

You are currently viewing የሴቶችን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የብድር አገልግሎቶች ማመቻቸቱን ስኬት ባንክ አስታወቀ

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

የሴቶችን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴቶችን ብቻ ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ የብድርና የባንክ አገልግሎቶች ማመቻቸቱን ስኬት ባንክ አስታውቋል፡፡

ባንኩ አለም አቀፉ የሴቶች ቀንን በተለያዩ መርሐ ግብሮች በዋና መስሪያ ቤቱ አክብሯል።

ስኬት ባንክ፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ እና ለማብቃት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ ወንድሙ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የባንኩ የሴት ደንበኞች ቁጥር ከግማሽ በላይ ደርሷል ያሉት ሃላፊዋ አብዛኛዎቹ የባንኩ ደንበኛ ሴቶች ከባንኩ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡:

ስኬት ባንክ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ሴቶች ውጤታማ ስራ ላይ ተሰማርተው እንዲሰሩ እንዳስቻላቸው በመጥቀስ ባንኩ የሴቶችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በቀጣይም የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ስኬት ባንክ ተደራሽነቱን በማስፋት ከ151 በላይ ቅርንጫፎችን መክፈቱንና አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review