የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይፈልጋል-ዶ/ር መቅደስ ዳባ

You are currently viewing የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይፈልጋል-ዶ/ር መቅደስ ዳባ

AMN – ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ “የሴቶች ጥቃት የእኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በጤና ሚኒስቴር ቅጥር ጊቢ ተከብሯል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ፣ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ቀን ስናከብር የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ አስፈላጊነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና የሴት ልጅ ጥቃት ለማስቆም በተለይ ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች ተገቢወን ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ተገቢውን የጤና እና ማህበራዊ አገልግሎት በመስጠት የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የአንድ መስኮት ማዕከላትን በአቅም እና በሰው ሀይል እንዲደራጁ እና ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ለማድርግ ተገቢው ትኩረት ተሰቶት እንደሚሰራበት ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ በበኩላቸው፣ እስከ ዛሬ ድረስ የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም የተለያዩ ስትራቴጂካዊ ስልቶች ተነድፈው እየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮ አመትም የጸረ ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ ቀን ስናከብር የሴቶችን ጥቃት ለማስቆም እንዲሁም በስራ ቦታ እና በተለያዩ መንገዶች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል እንዲቻል ያላቸውን ተጋላጭነት ሊቀንሱ የሚችሉ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review