የስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝ አጠናቀቁ

You are currently viewing የስሎቬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝ አጠናቀቁ

AMN ግንቦት 29/2017

ፕሬዝዳንቷ ወደሀገራቸው ሲመለሱም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው የሽኝት መርሃ ግብር አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጋር የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር በማጠናከር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ መምከራቸው ይታዎቃል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከፕሬዝዳንት ናታሻ ፒሪክ ሙሳር ጋር በብሔራዊ ቤተመንግስት በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያና ስሎቬንያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና በኅዋ ሳይንስ በትብብር ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንቷ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆንም ዘመናዊ የንብ ማነብ ሰርቶ ማሳያ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ማካሄዳቸው ይታወቃል።

እንዲሁም በኢትዮጵያ የነበራቸው ይፋዊ የስራ ቆይታ ንግድና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review