የስቅለት በዓልን ስናስብ የኢየሱስ ክርስቶስን የፅድቅ፣ የቅንነትና የደግነት ሀይል በማስታወስ በደልን በይቅርታ ልንሽር ይገባል-ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)

You are currently viewing የስቅለት በዓልን ስናስብ የኢየሱስ ክርስቶስን የፅድቅ፣ የቅንነትና የደግነት ሀይል በማስታወስ በደልን በይቅርታ ልንሽር ይገባል-ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 10/2017 ዓ.ም

የስቅለት በዓልን ስናስብ የኢየሱስ ክርስቶስን የፅድቅ፣ የቅንነትና የደግነት ሀይል በማስታወስ በደልን በይቅርታ ልንሽር ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ተከታዮች የስቅለት በዓልን በፀሎትና በዝማሬ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ስቃይ በማስታወስ አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር) ፤ በዓሉን የምናከብረው ፈጣሪ ላደረገልን የድህነት ስራ አምላክን ለማመስገንና ለማክበር ነው ብለዋል፡፡

የስቅለት ቀን ስናስብ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና መከራን ከፍሎ የሰው ልጆችን ከሞት ወደ ህይወት ያመጣን እራሱን መስዋዕት አድርጎ የክፋትን ስራ በትንሳኤው ድል መንሳቱን በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን የፅድቅ፣ የቅንነትና የደግነት ሀይል ለማስታወስ በደልን በይቅርታ መሻር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር በመስዋዕትነቱ የገለፀበት ይህ የስቅለት ቀን፤ ለሌሎች መስዋዕት መሆንን የሚያስተምር ነው ሲሉም የበዓሉ ታዳሚ ምዕመናን አንስተዋል፡፡

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review