የስንዴ ዱቄት ማበልጸግ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ሥርዓት ሊተገበር ይገባል-ባለስልጣኑ

You are currently viewing የስንዴ ዱቄት ማበልጸግ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ሥርዓት ሊተገበር ይገባል-ባለስልጣኑ

AMN – ሚያዚያ 2/2017 ዓ.ም

ጤናማና አምራች ትውልድ ለማፍራት የስንዴ ዱቄት ማበልጸግ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ሥርዓት እንዲተገበር የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አሳሰበ።

ያልተመጣጠነ ምግብ መመገብ በሰዎች ጤናና አእምሮ ዕድገት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ የዘርፉ ባለሙያዎች ያነሳሉ።

በኢትዮጵያ ጤናማና አምራች ዜጋ ለማፍራት ህብረተሰቡ በዕለት ተዕለት የሚጠቀማቸው የምግብ ዓይነቶች በንጥረ ነገር የበለጸጉ እንዲሆኑ አስገዳጅ መመሪያ ወጥቷል።

ከእነዚህም መካከል የምግብ ዘይትና የስንዴ ዱቄት ዋነኞቹ ናቸው።

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የሥራ ኃላፊዎች፣ ይህ ውሳኔ ጤናማ፣ ንቁ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ጥረትና ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።

በባለስልጣኑ የምግብ ምዝገባና ፍቃድ መሪ ሥራ አስፈፃሚ መንግስቱ አስፋው፣ ዘይትና የስንዴ ዱቄት በንጥረ-ነገር እንዲበለፅጉ በደረጃዎች ምክር ቤት ውሳኔ ተሰጥቶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

በምርቶቹ ላይ አስገዳጅ መመሪያ መውጣቱን ተከትሎ ባለስልጣኑ ፍቃድ ለሰጣቸው አምራቾች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን ሲሰጥ መቆየቱንም ገልጸዋል።

በባለስልጣኑ የምግብ ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም መሪ ስራ አስፈፃሚ ሙላቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ለህብረተሰቡ ጤናና ምርታማነት ሲባል ሁሉም ዓይነት የምግብ ዘይትና የስንዴ ዱቄት መበልጸግ እንዳለበት አስረድተዋል።

ይሁንና አምራቾች የተሰጣቸውን የዝግጅት ጊዜ ቢጨርሱም ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ባለመግባታቸው ቁጥጥር እየተደረገ በየጊዜው ማስጠንቀቂያ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review