የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢሎን መስክ የንግድ የጠፈር ኩባንያ የሆነዉ ስፔስ ኤክስ ፤ መንኮራኩር ለማምጠቅ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
መንኮራኩሩ ቴክሳስ ከሚገኘው የሮኬት ማስወንጨፊያ ከተወነጨፈ ከ30 ደቂቃ በኋላ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሽክርክሪትና መበታተን ያጋጠመው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
የችግሩ መንስኤ የነዳጅ መፍሰስ መሆኑ ታውቋል።
403 ጫማ ርዝማኔ ያለው ሮኬቱ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ካለፉት ያልተሳኩ ሙከራዎች የተሻለ ርቀት መጓዙ ተገልጿል፡፡
ስፔስኤክስ ለዘጠኝ ጊዜአት ካደረገዉ ሙከራዎች አምስቱ አለመሳካታቸዉ ተነግሯል፡፡
የመንኮራኩሩ ፍርስራሽ በደቡብ አሜሪካ ግዛቶች እና የአየር መንገድ አካባቢዎች ተበታትኖ የተገኘ ሲሆን የአሜሪካ ብሄራዊ አሺዬሽንም ከዚሁ ፍርስራሽ ጋር በተያያዘ አንዳንድ በረራዎች አቅጣጫ እንዲቀይሩ ማድረጉን አልጀዚራ ዘግቧል።
ኢሎን መስክ ሙከራዎቹ የስፔስኤክስ ማርስን የመያዝ እቅድ አንዱ አካል እንደሆነ ተናግሯል።
ድርጅቱ ከ50 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎችን በጨረቃ ላይ ለማስፈር ከናሳ ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል።
በሊያት ካሳሁን