
AMN ኅዳር -29/2017 ዓ.ም
በሶሪያ የሚገኙ የአማጺያን ኃይሎች ዋና ከተማዋን ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ አገር ጥለው መሰደዳቸውን አስታውቀዋል፡፡
በሽር አል-አሳድ ወደ ማይታወቅ ቦታ ከደማስቆ በአውሮፕላን እንደወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡
የሃያት ታህሪር አል-ሻም አዛዥ አቡ ሞሐመድ አል ጁላኒ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ለጊዜው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል እንዲመሩ አዘዋል፡፡
የሶሪያ አማፂያን ዋና ከተማዋን ደማስቆን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ህዝቡ በአደባባይ ደስታውን እየገለጸ መሆኑንም ዘገባው ያሳያል፡፡
የ59 ዓመቱ ባሽር አል-አሳድ ስልጣን የተረከቡት ከ1971 ዓ.ም. ጀምሮ ሀገሪቱን የመሩት አባታቸው ሃፌዝ አል-አሳድ መሞታቸውን ተከትሎ እ.ኤ.አ በ2000 እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል።