AMN ህዳር 19/2017 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በአልን አስመልክቶ የፎቶ አውደርእይ በሳይንስ ሙዝየም ተከፈቷል።
የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሀሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።
በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገርን ጨምሮ የፓርቲው እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
በአውደርእዩ ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ምስሎች ቀርበውበታል።
አውደርእዩ እስከነገ ድረስ እንደሚቆይም ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።