የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ይካሄዳል – አቶ አደም ፋራህ

You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ይካሄዳል – አቶ አደም ፋራህ

AMN-ታህሣሥ 16/2017 ዓ.ም

2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

በአንደኛው ታሪካዊ የብልጽግና ፓርቲ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን በመፈጸም በኩል አበረታች ሥራዎች መፈጸማቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

ባለፈው የፓርቲው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ፣ በአሰባሳቢ ትርክት ማዳበር፣ በሰላም እና ደህንነት እና በመሰል ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመፈጸም ፓርቲው ለሕዝብ የገባቸውን ቃሎች በማክበር እና በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በኢኮኖሚው የሃገር በቅል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በመተግበር እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመተግበር ተጨባጭ ለውጥ የታየባቸው ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ጠቅሰዋል።

የአቅም መገንባት ስራዎች መሰራታቸውን አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የማበረታቻ እና የእርምት እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ጠንካራ የፌደራል ስርዓት እንዲፈጠር መሰራቱን ጠቅሰዋል።

የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አንጻርም አበረታች ሥራዎች መሰራታቸውን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርበው የሚነጋገሩበት ምህዳር መፈጠሩን አንስተዋል።

በሂደቱ ያጋጠሙ ከሰላም ከጽንፈኝነት ጋር የተያያዙ እና መሰል ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን በመቋቋም ሥኬቶች መመዝገባቸውንም ተናግረዋል።

ለ2ኛው ጉባኤ ዝግጅትም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን መናገራቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ማኀበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

AMN- Mudde

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review