የብልፅግና ፓርቲ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

በአጠቃላይ ሀገራዊ ፓለቲካ ሁኔታ፣ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለማሳካትና በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ አጀንዳዎችን የሚገመግመው መድረክ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ተጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የዘርፍ አመራሮች የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል የአደረጃጀት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለ3 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንትና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፣ በመድረኩ የፓርቲ መደበኛ ስራዎች፣ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ግብረ መልስ እና በየክልሉ ያሉ የፓለቲካ አዝማሚያ ግምገማ እንደሚደረግ አንስተዋለ።

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በየደረጃው የተደረጉ ውይይቶች አፈጻጸም በተመለከተ ውይይት ይደረጋልም ብለዋል።

በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ የሚደረግ መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በስራ እድል ፈጠራ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ስራዎች እና ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ያሉበት ደረጃ በስፋት የሚገመገም መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review